Quantcast
Channel: Planet Ethiopia.com - RSS Feed
Viewing all articles
Browse latest Browse all 19220

በፍቅረኝነት ዘመናቸው ይገናኙበት የነበረው ቦታ ላይ ፍቅረኛውን ከ20 ዓመታት በላይ የጠበቀው የለማ ኃይሌ ታሪክ…

$
0
0

በፍቅረኝነት ዘመናቸው ይገናኙበት የነበረው ቦታ ላይ ፍቅረኛውን ከ20 ዓመታት በላይ የጠበቀው የለማ ኃይሌ ታሪክ…

“ቢያልፍም ጊዜም ቢነጉድም፣
ሌላ እኔ አልለምድም…”

የታሪኩ መነሻ ከዛሬ 20 ዓመታት በፊት ነው - እዚሁ አዲስ አበባ ጎፋ ካምፕ፡፡ የያኔው ወጣት ለማ ኃይሌ አንዲት ፍቅረኛ ነበረችው፡፡ ድንገት ታዲያ የዚህን ወጣት ልብ የሰበረ ክስተት ተከሰተ - ፍቅረኛው ባልታወቀ ምክንያት ወደ ሰሜን አሜሪካ ነጎደች፡፡

ከፍቅረኛው መለየቱን መቋቋም የተሳነው ለማ ታዲያ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ከ20 ዓመታት በላይ በየቀኑ ያኔ በፍቅረኝነት ዘመናቸው ይጠብቃት፣ ይሸኛት የነበረው መንገድ ላይ ይቆማል፡፡

ከዓመታት በኋላ ከጎፋ ሰፈር ለቅቀው ለቡ የገቡት የለማ ቤተሰቦችም ታዲያ ሁሌ ጠዋት በመኪና እዚያው የሚቆምበት ቦታ ያደርሱታል፤ ማታ ላይ ይመልሱታል፡፡ የልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ እንደሚነግረን ወደ ሰሜን አሜሪካ የሄደቸው ፍቅረኛው ከ11 ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥታ ለማን የቆመበት ቦታ ብታገኘውም እሱ ግን አልለያትም ይለናል፡፡

ትዳር መስርታ የልጆች እናት የሆነቸው የያኔው ፍቅረኛው እንባዋን ረጭታ ወደ ሰሜን አሜሪካ ተመለሰች፡፡

ይህን አሳዛኝ ታሪክ የሰማው የግጥምና ዜማ ደራሲው አማኑዔል ይልማ፣ “ይለፍ እድሜ” በሚል ርዕስ የጻፈውን ግጥም ኃይለየሱስ ግርማ ባማረ መልኩ ተጫውቶታል፡፡

“በሌለሽበት ቦታ - ብቻዬን ተጉዤ፣
ሲመሽ እመለሳለሁ - ሐሳብ ትዝታሽን ይዤ፣
የቆምኩበት ቀርቶ ትዝታሽ፣
ያመላልሰኛል ባትኖሪ እንኳ በጭራሽ፣
ዝንታለም ቢያልፍ ዕድሜ በተርታ፣
እኔ ግን ከዚያው ነኝ ከተውሽኝ ቦታ፣
ቢያልፈኝ ጊዜው ቢነጉድም፣
ሌላ እኔ አልለምድም፣
ይለፍ ጊዜ ይለፍ እድሜ፣
እንቺን ስል ቆሜ…
ሰማይ ምድር ቢያልፍ ቃሉ እንደማይጠፋ፣
በቃልሽ እጸናለሁ ይህ ነው የኔ ተስፋ፣
ተራራውም ቢሸሽ - ባህርም ወጥቶ ቢፈስ…
እኔ ግን ከዚያው ነኝ አይጨንቀኝም የነፍስ፣
ቢያልፍም ጊዜም ቢነጉድም፣
ሌላ እኔ አልለምድም…”

Viewing all articles
Browse latest Browse all 19220

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>